• Organic Agriculture
    Organic Agriculture

Farmer Kassu Aragaw’s Success at Organic Farming

የአርሶ አደር ካሱ ስኬት በተፈጥሮአዊ ግብርና

DSC 0058

 

በኦሮሚያ ክልል የሪቄቻ የተፈጥሮ አትክልት አምራቾች ማህበር አባል የሆኑት አቶ ካሱ አራጋው የተፈጥሮአዊ ግብርናና መሰል ስራቸውን እንደሚከተለው ይገልፃሉ፡-

የእኔ ማህበር ይላሉ አርሶ አደር ካሱ "የሪቄቻ የተፈጥሮ አትክልት አምራቾች ማህበር"; የተፈጥሮ ግብርናን እንዴት እንደ ጀመረ ሲገልጹ:: "ማህበራችን ከሰባት ዓመት በፊት ነበር በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት የሚተገበረውን የተፈጥሮ ግብርና ፕሮጀክት የተቀላቀለው ፡፡ የማህበሩ አባላት የሆንን በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት የሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎችን ከወሰድን በኋላ የተፈጥሮ ግብርናን በተግባር ያዋለ በሆለታ የመጀመሪያው ማህበር ነው፡፡ በመጀመሪያ ለሙከራ ብለን ኮምፖስት አዘጋጅተን በ 300m2 መሬት ላይ በመበተን የተፈጥሮ ግብርናን በበር ተክሎች እንደ ባቄላ የመሳሰሉትን በመትከል ጀመርን። 

 

እንዲሁም እንደ ጎመን፣ ቀይስር፣ ቆስጣ ያሉ የጓሮ አትክልት አምርተን አበረታች የሆነ ውጤት አየን ፡፡ በተለይም የቀይ ስር ምርት ከፍተኛ ነበር ፡፡ ውጤቱን ካየን በኋላ ነው ማሳችንን በሙሉ በተፈጥሮ ግብርና ዘዴ ተጠቅመን በሰፊው ኮምፖስት በማዘጋጀት ማምረት እንዳለብን ወስነን ወደስራ የገባነው፡፡ በአሁኑ ወቅት 7750m2 የሆነውን የእርሻ መሬታችንን ምንም አይነት ኬሚካል ሳንጠቀም የተፈጥሮ ግብርና ዘዴዎችን በመጠቀም እያመረትን እንገኛለን ፡፡ ሰባታችንም የማህበሩ አባላት መሬቱን እኩል ተካፍለን ነው እያመረትን የምንገኘው ከዛ ውስጥ የእኔ ድርሻ 1107.14m2 ነው ፡፡ ሁላችንም የተፈጥሮ ግብዓቶችን በመጠቀም፣ ኮምፓስትን በማዘጋጀት ነው እያመረትን የምንገኘው ፡፡ ከዋናው ኮምፖስት ማዘጋጀት በተጨማሪ ግርማ ዘውዴ የተባለ አርሶአደር እና እኔ ስለ ቨርሚ ኮምፖስት ባገኘነው ስልጠና እና አምቦ ሄደን ባየነው ተሞክሮ መሰረት ቨርሚ ኮምፖስት እያዘጋጀን የማሳችን አፈር ለምነት እንዲጨምር እየሰራን ነው ፡፡ ሌሎች የማህበራችን አባላት የአኛን ውጤት በማየት አሁን ቨርሚ ኮምፖስትንም ማዘጋጀትና መጠቀም ጀምረዋል"፡፡;

አርሶአደር ካሱ እና የማህበራቸው አባላት የአፈር ለምነትን ከመጠበቅ አንፃር ሌላው እየተገበሩ የሚገኙት ደግሞ የተለያዩ አትክልቶችንና ሰብሎችን አፈራርቆ መዝራትን በመተግበር ነው፡፡ በዚህም ምርታቸውን በማሻሻል ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት በሚተገበረው የተፈጥሮአዊ ግብርና አመራረት ፕሮጀክት በመታቀፋቸው ሌላው ያገኙትን ውጤት ሲገልፁ "ፕሮጀክቱ የገበያ ትስስርን ፈጥሮልን አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ መዳረሻ አካባቢ በየአስራ አምስት ቀን ቅዳሜ ምርቶቻችንን ማለትም የጓሮ አትክልቶችን እየወሰድን በመሸጥ ገቢያችን እየተሻሻለ ነው፡፡ «የተፈጥሮአዊ ዘዴ አምራች አርሶአደሮች የገበያ ቀን» በሚል ከሃምሌ ወር 2010 ጀምሮ በተጀመረው የገበያ ትስስር በቋሚነት እስካሁን ድረስ እንደ ቲማቲም፣ ድንች፣ ዝኩኒ፣ ቀይስር፣ ካሮት፣ ቆስጣ፣ ጎመን የመሳሰሉትን እያቀረብን እንገኛለን"፡፡ አሁን ላይ በተፈጥሮአዊ ዘዴ እና በኬሚካል ግብአቶች በመጠቀም በሚመረቱ ምርቶች ላይ ያለውን ልዩነት ማህበረሰቡ በመገንዘቡ እና ገበያውም ስለተለመደ ምርታቸውን በጥሩ ዋጋ እየሸጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ስለዚህም የተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የማህበሩ አባላት ገቢያቸው እንዳደገ በዚህም በቤተሰቦቻቸው ኑሮ ላይ መሻሻል እንደታየ ተናግረዋል፡፡ አሁን ምርቶቻቸውን በቋሚነት የሚወስዱላቸው ደንበኞች አፍርተዋል፡፡ ከጅምሩ አዲስ አበባ የተፈጥሮ ግብርና የገበያ ቀን ፕሮግራም ላይ ምርቶቻቸውን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት የትራንስፖርት እና የተለያዩ ወጪዎችን ዘላቂ ልማት ነበር ይሸፍን የነበረው በሂደት ገቢያቸው እየተሸሻለ በመሄዱ ወጪዎቻቸውን በራሳቸው መሸፈን ጀምረዋል፡፡

አርሶአደር ካሱ ሲናገሩ ዝናብ በሌለ ጊዜ ከማሳቸው አጠገብ ካለው ወንዝ በእቃ ቀድተው እያጠጡ ነበር ሲያመርቱ የቆዩት ነገር ግን በገበያ ትስስሩ አማካኝነት ባገኙት የተሻለ ገቢ ባለፈው ጥር 2012 የራሳቸውን የውሃ መሳቢያ ሞተር በ9500 ብር ገዝተው ጊዜአቸውንም ጉልበታቸውንም ለመቆጠብ ችለዋል ፡፡ በዚህም ከበፊቱ የበለጠ ምርት ማምረት አስችሎአቸዋል፡፡

በተጨማሪም ከእርሻቸው አካባቢ ያለው የብዝሀ ሕይወት አጠባበቅም እንዲጨምር አድርገዋል፡፡ በአቅራቢያው ባለው ወንዝ ዙሪያ ዛፎችን በመትከል የነበሩትንም ጥበቃ በማድርግ የአፈር መሸርሸርን እየተከላከሉ ለአየር ንብረት ጥበቃም አስተዋፅኦ እንዲያደርግ እየሰሩ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡ ምክንያቱም የአየር ንብረት ለውጥ፣ ጎርፍ እና በተክሎቻቸው ላይ የሚከሰት በሽታ ካሉባቸው ተግዳሮቶች ዋነኞቹ ስለሆኑ ነው፡፡

በመጨረሻም ካሱ "ስልጠናዎች እና ልዩ ልዩ ድጋፎች ከማግኘት በተጨማሪ ቁርጠኝነት እና ጠንክሮ መሥራት ያስፈልጋል ለዚህም የተሻለ ምርትና ገቢ ለማግኘት እኔም ሆንኩ የማህበራችን አባላት የበለጠ ጠንክረን እየሰራን ነው" ብለዋል፡፡

አርሶአደር ካሱ ዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ስልጠና በመስጠት፣ የልምድ ልውውጥ በማመቻቸት እና በተለይም የገበያ ትስስር በመፍጠር ለውጥ እንድናመጣ ስላደረገን በከፍተኛ ደረጃ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

 

Farmer Kassu Aragaw’s Success at Organic Farming

Kassu Aragaw one of the members of Rikecha Organic Vegetable Producers Association in Holeta town, Oromia region, described his organic work as follows:

“My association, Rikecha Organic Vegetable Producers Association, said farmer Kassu, “joined the organic farming project implemented by the Institute for Sustainable Development seven years ago. It was the first association to put organic farming into practice after various training activities were conducted for us by ISD. We started practicing organic farming after preparing compost and applying it on 300m2 of land by first planting leguminous plants Faba Bean. We planted cabbage, beetroot, and Swiss chard. The result was encouraging, with beetroot yield particularly high. After observing these promising results we decided to continue practicing organic agriculture and transforming our farmland into an organic farming area. At present, the whole farmland which is 7750m2 is now an organic farming area”.

Seven members of the association share the farmland equally. Kassu’s share is 1107.14m2. All the farmers have agreed to use natural inputs. The members prepare compost and apply it to their farms. Girma Zewdie and Kassu also prepare vermicompost and, by planting different types of vegetables and herbs using crop rotation, have been successful in restoring the soil’s fertility.

Kassu also commented on how the project created market linkage opportunities in Addis Ababa for him and other farmers. He said “I am actively participating in an Organic Farmers’ Market Day by selling different types of organic vegetables and herbs. I collect the organic produce from the members and sell them in the market in Addis Ababa. The Organic Farmers’ Market Day has helped me obtain more income and has transformed the livelihood of my family and that of members of the association. I have also started selling organic potato seed”.

Market linkage activities in Addis Ababa first began in July 2018 at Natani Café and Restaurant near Bole International Airport. The market day occurs every two weeks on Saturday mornings. Organic farmers from Holeta town, Oromia Region, sell different types of vegetables such as potatoes, carrots, Swiss chard, zucchini, spinach cabbage, beetroot, lettuce, and herbs. The market day opportunity has helped farmers earn more income by selling their produce at good prices.

“Kassu said “by becoming organic farmers we could change the fertility of the soil, increase productivity, feed our families healthy foods, and transform our livelihood, all by taking advantage of the market day opportunity in Addis Ababa. We now have customers who regularly purchase our produce”.

In January 2020 Kassu bought his own water pump generator to pump water from the nearby river to his farm. Also in the same month when the sun was out and with the help of irrigation and his pump, he managed to produce a variety of vegetables, including Swiss chard, spinach, lettuce, potatoes, beetroot, carrots, zucchini, and herbs. Kassu pointed out, however, that there were challenges he had had to contend with such as diseases and climate change, the latter resulting in flooding. “Biodiversity preservation adjacent to our farm has increased”, said Kassu. He and other members planted trees around the river to help reduce soil erosion.

Kassu told us that training received from ISD, plus in addition to the experience sharing, and particularly market linkage opportunities in Addis Ababa have been greatly appreciated. He added that since January 2020 ISD has stopped sharing the cost of transporting food items from Holeta to Addis Ababa, as well as covering the cost of table rent for displaying the produce. “This has enabled us to meet the full cost of transportation and table rent ourselves, mostly by selling our produce in Addis Ababa at good prices”, said Kassu.

In conclusion, Kassu said, “Bearing the label “organic” and undergoing training is not enough to be successful. Commitment and hard work are required. That is why I work hard!!”